የሀገር ውስጥ ዜና

የመከላከያ ዋር ኮሌጅ በመደበኛ ኮርስ ያሰለጠናቸውን ከፍተኛ መኮንኖች እያስመረቀ ነው

By Yonas Getnet

June 22, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ለ3ኛ ጊዜ በመደበኛ ኮርስ ያሰለጠናቸውን ከፍተኛ ወታደራዊና የጸጥታ ዘርፍ አመራሮችን እያስመረቀ ነው።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ፣ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ ዲፕሎማቶች እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።

የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ዋና አዛዥ ብ/ጀ ቡልቲ ታደሰ ፥ በሰላማዊ፣ ዲፕሎማሲያዊና በወንድማማችነት መርህ የኢትዮጵያን ጥቅም ለማስጠበቅ የሚያስችል የአመራር መርህን በመከተል ፕሮፌሽናል ሰራዊት ግንባታ ሥራ ላይ በተደራጀ መንገድ መሥራት ይገባል።

በቀጣናው ያለው ያልተረጋጋ ሁኔታ እና በኢትዮጵያ ላይ እየሆነ ባለው የውስጥ ግጭት ጠማቂዎች እየሸረቡት ያለው ሴራ ቀላል አለመሆኑን አንስተዋል፡፡

ይህን በመረዳት የትምህርትና ስልጠና ተቋማት፣ ምሁራን እና የምርምር ተቋማት የተወሳሰበውን ሁኔታ ጥናትና ምርምር በማድረግ ለፖሊሲዎችና ስትራቴጅዎች ግብዓት የሚሆን ሃሳብ ማመንጨት አለባቸው ብለዋል።

በመሳፍንት ብርሌ