አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ በቴክኒክ ሙያ ዘርፍ የዶክትሬት ዲግሪ (ሌቪል 8) ትምህርት ስልጠና ለመስጠት ዝግጅት ተጠናቅቋል አሉ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል።
የኢፌዴሪ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡
ወ/ሮ ሙፈሪሃት በዚህ ወቅት እንዳሉት÷የሀገሪቱን ሁለንተናዊ ዕድገት ለማረጋገጥ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዘርፍ ወሳኝ ነው ።
መንግስት ዘርፉን በማጠናከር ዓለም የደረሰበት ደረጃ ለማድረስ ባለፉት ዓመታት በርካታ ተግባራትን ማከናወኑን አንስተዋል።
ይህንን ተከትሎ ዘርፉ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ማግኘቱን ጠቅሰው ÷ በ2017 የዓለም አቀፍ የክህሎት ህብረተሰብ አባል መሆን የተቻለበት ውጤታማ ዓመት መሆኑን ተናግረዋል።
ዘርፉ የሀገርን ብልጽግና ለማረጋገጥ ወሳኝ በመሆኑ በቀጣይም የተገኘውን ውጤት ይበልጥ ለማጠናከር በትኩረት ይሰራል ነው ያሉት።
በቀጣይ ዓመት በሌቭል 8 ዶክትሬት ዲግሪ ትምህርት ለመጀመር ዝግጅት የተጠናቀቀ ሲሆን÷ ይህም ዘርፉን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ያስችላል ብለዋል።
የዛሬ ተመራቂ ተማሪዎች በሰለጡኑበት ዘርፍ ሀገራቸውን እና ሕዝባቸውን በታታሪነት እንዲያገለግሉ ሚኒስትሯ ጥሪ ማቅረባቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!