አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት እስካሁን በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች 34 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶችን በመገንባት ለአገልግሎት አብቅቻለሁ አለ፡፡
ጽ/ቤቱ ከዩኤንኤፍፒኤ ጋር በመተባበር የወር አበባ ንጽህና አጠባበቅ ቀንን በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በተሰራው ብርሃን የአይነ ስውራን 2ኛ ደረጃ አዳሪ ት/ቤት ውስጥ አክብሯል፡፡
የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት እንደ ሀገር እስካሁን 34 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶችን በመላ ሀገሪቱ በመስራት በርካታ ተማሪዎች በአቅራቢያቸው ጥራት ያለው ትምህርት እንዲያገኙ ሰፊ ሥራ አከናውኗል፡፡
ሴት ተማሪዎች ተፈጥሯዊ በሆነው በወር አበባ ምክንያት በጤናቸው፣ በንጽህናቸውና በትምህርታቸው ላይ ችግር እንዳይገጥማቸው ለማስቻል የተሟላ የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ ኪቶችን ለሴት ተማሪዎች በስፋት ድጋፍ እያደረገም ይገኛል፡፡
በበዓሉ ላይ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት፣ተማሪዎች፣ መምህራን እና የት/ቤቱ ማህበረሰብ መገኘታቸውን የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
በመርሐ ግብሩ በባለሙያዎች እና በተማሪዎች አዘጋጅ እና አቅራቢነት በወር አበባ ንጽህና አጠባበቅና ተያያዥ ርዕሶች ዙሪያ የተለያዩ ግንዛቤ ማሳደጊያ መልዕክቶች ተላልፈዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!