የሀገር ውስጥ ዜና

5 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር በሬሚታንስ ወደ ሀገር ተላከ

By Melaku Gedif

June 23, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ከውጭ ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ በሬሚታንስ 5 ነጥብ1 ቢሊየን ዶላር ተልኳል አለ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት፡፡

የአገልግሎቱ የፕላን ክፍል ሃላፊ ወንድወሰን ተረፈ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ የዳያስፖራውን ሁለንተናዊ ተሳትፎ ለማጠናከር በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡

በበጀት ዓመቱ ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ጋር ተያይዞ ዳያስፖራው ወደ ሀገር የሚልከው ሬሚታንስ እንዲጨምር ትኩረት ተሰጥቶ መሰራቱን ተናግረዋል፡፡

ዳያስፖራው የውጭ ምንዛሬ አካውንት እንዲከፍት መደረጉን ጠቁመው÷ በዚህም 18 ሺህ 889 አካውንት ማስከፈት ተችሏል ነው ያሉት፡፡

በተከፈተው አካውንትም 25 ነጥብ 2 ሚሊየን ዶላር መቆጠቡን ያነሱት ሃላፊው ÷ ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጻር ከፍተኛ እድገት ማሳየቱን አስረድተዋል፡፡

በሌላ በኩል ከዳያስፖራ የሚገኘውን ሬሚታንስ ለማሳደግ በተደረገው ድጋፍና ክትትል 5 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር በሬሚታንስ ወደ ሀገር መላኩን ጠቅሰዋል፡፡

ለሬሚታንስ መጨመር በኢትዮጵያ የተደረገው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!