አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ-አሜሪካ የቢዝነስ ጉባዔ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎችና የአሜሪካ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በአንጎላ ሉዋንዳ በይፋ ተጀምሯል።
በጉባዔው በፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡
በመርሐ ግብሩ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች፣ ሚኒስትሮች፣ የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የአሜሪካ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጨምሮ 1 ሺህ 500 ተሳታፊዎች ታድመዋል፡፡
ጉባዔው በአፍሪካና በአሜሪካ መካከል ያለውን የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር በሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች ላይ ቀጣይ አቅጣጫዎችን እንደሚያስቀምጥ ታምኖበታል።
ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በጉባዔው ንግግር የሚያደርጉ ሲሆን÷ ከጉባዔው ጎን ለጎንም የተለያዩ የሁለትዮሽ ውይይቶችን እንደሚያካሂዱ የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!