አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በዛሬው ዕለት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሦስት ዓመት ሕጻንን ጨምሮ የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ አደጋው በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 3 በተለምዶ አባሳሙኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው የተከሰተው፡፡
ከኃይሌ ጋርመንት ወደ ዩኒሳ አደባባይ ይጓዝ የነበረ የፐብሊክ ሰርቪስ አውቶቡስ ከከባድ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ መንገድ ስቶ ወደ ተቃራኒ አቅጣጫ መግባቱን አብራርተዋል፡፡
ይህን ተከትሎም አውቶቡሱ ወደ ተቃራኒ አቅጣጫ ከገባ በኋላ ከዩኒሳ አደባባይ ወደ ኃይሌ ጋርመንት ሲጓዝ ከነበረ ዶልፊን ተሽከርካሪ ጋር መጋጨቱን ነው የገለጹት፡፡
በዚህም በዶልፊኑ ውስጥ ከነበሩት ተሳፋሪዎች መካከል አሽከርካሪውን ጨምሮ የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት ማለፉን ተናግረዋል፡፡
ከሟቶቹ መካከል የ3 ዓመት ሕጻን እንደሚገኝ ጠቁመው÷ በአደጋው 8 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን አመልክተዋል፡
በመላኩ ገድፍ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!