የሀገር ውስጥ ዜና

አዲስ አበባን ጨምሮ በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች ኤሌክትሪክ ተቋርጧል

By Melaku Gedif

June 23, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አዲስ አበባን ጨምሮ በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡

የአገልግሎቱ የኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ አቶ አንዋር አብራር ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ የኤሌክትሪክ ሃይል በከፊል የተቋረጠው ከዋናው ግሪድ ባጋጠመ የቴክኒክ ቸግር ምክንያት ነው፡፡

አሁን ላይም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያጋጠመውን ብልሽት ለማስተካከል ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ እንደሚገኝ ነው ያስረዱት፡፡

ለተፈጠረው ችግር ደንበኞችን ይቅርታ የጠየቁት አቶ አንዋር÷ በትዕግስት እንዲጠብቁንም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡- YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook WMCC TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!