የሀገር ውስጥ ዜና

የአካባቢውን ታሪክና የተፈጥሮ ጸጋ ያጣመረው ሀላላ ኬላ ሪዞርት…

By Adimasu Aragawu

June 24, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የመንግስት እና የግሉ ዘርፍ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች የሀላላ ኬላ ሪዞርትን ጎብኝተዋል።

ባለሙያዎቹ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር ከተወያዩ በኋላ ነው ዳውሮ ዞን የሚገኘውን ሀላላ ኬላ የጎበኙት፡፡

የገበታ ለሀገር ኮይሻ ፕሮጀክት አካል የሆነው ሀላላ ኬላ ሪዞርት የአካባቢውን ታሪክ እና የተፈጥሮ ጸጋ አጣምሮ የያዘ ውብ ስፍራ ነው።

ባለሙያዎቹ የጊቤ ሦስት የኃይል ማመንጫ የፈጠረውን ሰው ሰራሽ ሃይቅ የመስህብ ሥፍራ እና የንጉስ ሀላላ ካብንም ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡

ሀላላ ኬላ ሪዞርት ዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቁ የመዝናኛ ሥፍራዎች፣ ባሕላዊ እና ታሪካዊ ቅርሶችን የያዘ ሙዚዬም እንዲሁም መሰብሰቢያ አዳራሾችን አካትቶ ይዟል፡፡

ሪዞርቱ የዳውሮ ሕዝብ ጥንታዊ የካባ አሰራር መልክን የገለጠ እና የሀገርን ጸጋ ወደ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የቀየረ መሆኑን የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ተናግረዋል።

ፕሮጀክቱ ለአካባቢው ወጣቶች የሥራ እድል በመፍጠር ረገድ በሰው ሰራሽ ሐይቁ በአሳ ማጥመድ እና ጀልባ ሽርሽር ተደራጅተው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስቻሉ የሚበረታታ ነው ብለዋል።

መንግስት በብዝሃ ዘርፍ ኢኮኖሚ ለቱሪዝም ዘርፍ የሰጠው ትኩረት ውጤታማነት ማሳያ አንዱ ምልክት ሀላላ ኬላ እንደሆነም ባለሙያዎቹ አብራርተዋል።

በኃይለኢየሱስ መኮንን

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!