አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሶማሌ ክልል የገቢዎች ቢሮ ባለፉት 11 ወራት ከ16 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ሰብስቧል።
የቢሮው ኃላፊ አቶ መሀመድ አብዲ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ በበጀት ዓመቱ 17 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ እስካሁን ከ16 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ለመሰብሰብ ተችሏል።
በክልሉ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተውጣጣ ግብረ ኃይል በማቋቋም በተሰራው ስራ የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን ጠቁመዋል።
ለልማት፣ ለሰላም እና ለሌሎች ጉዳዮች ገቢ መሰብሰብ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዳለው አንስተው÷ ኅብረተሰቡ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል።
በዮናስ ጌትነት