የሀገር ውስጥ ዜና

ቱሪዝምን ከግብርና ያስተሳሰረው ቤኑና መንደር…

By Adimasu Aragawu

June 24, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከመንግስት እና ከግል ሚዲያ ተቋማት የተወጣጡ የሚዲያ ባለሙያዎቸ በበሰቃ ሃይቅ ዳርቻ የተገነባውን የቤኑና መንደር ጎብኝተዋል።

የቤኑና መንደር እጅግ ዘመናዊ መኝታ ክፍሎች፣ አዳራሽ፣ ሲኒማ ቤት የመዝናኛ ሥፍራዎች፣ ስፓ እንዲሁም የፍራፍሬ ልማትና የሌማት ትሩፋትን አካትቶ ይዟል፡፡

የመንደሩ ግንባታ ባሕላዊ የኪነ ሕንጻ ጥበብን ከዘመናዊ ግንባታ ጋር አቀናጅቶ የያዘ ሲሆን÷ ለአካባቢው ተጨማሪ የቱሪዝም አቅም የፈጠረ ውብ መዳረሻም ነው፡፡

የሚዲያ ባለሙያዎች በጉብኝታቸው ወቅት ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት ÷ መንደሩ ለምነት የራቀውን መሬት ወደ አረንጓዴነት የቀየረ ነው።

ሀሳብ ካለ የትኛውንም አስቸጋሪ ሁኔታ መሻገር እንደሚቻል አመላካች ነው ያሉት ባለሙያዎቹ÷ የቤኑና መንደር ማንኛውንም ነገር ማድረግ እና ሕልምን መተግበር እንደሚቻል ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

የቤኑና መንደር ቱሪዝምን ከግብርና ጋር ያስተሳሰረ መሆኑን አንስተው÷ እንደ ሀገር የተወጠኑ የግብርና ኢኒሼቲቮችን ዕውን ከማድረግ አንጻር በጎ ሚና ይኖረዋል ነው ያሉት።

በተለያዩ አካባቢዎች እየተገነቡ የሚገኙ መሰል የቱሪዝም መዳረሻዎችን በማስተዋወቅ የኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እንዲኖራቸው መገናኛ ብዙሃን ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል።

በወንድሙ አዱኛ

 

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!