የሀገር ውስጥ ዜና

ባሕላዊ የግጭት አፈታት ሥርዓት የፍትሕ ተደራሽነትን እያሳደገ ነው

By Melaku Gedif

June 24, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ባሕላዊ የግጭት አፈታት ሥርዓት የፍትሕ ተደራሽነትን እያሳደገ ነው አሉ የፍትሕ ሚኒስትር ሀና አርአያስላሴ።

በኢትዮጵያ የሕግ ሥርዓት ውስጥ ባሕላዊ የግጭት መፍቻ ዘዴን ለማካተት መወሰድ በሚገባቸው ርምጃዎች ላይ ያተኮረ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

ወ/ሮ ሃና አርአያስላሴ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በኢትዮጵያ ላለፉት ዓመታት ግጭቶች በባሕላዊ የፍትሕ ሥርዓት ሲፈቱ ቆይተዋል።

ሕብረተሰቡ ለበርካታ ዘመናት ሲጠቀምባቸው የቆዩ ባሕላዊ የግጭት አፈታት ሥርዓቶች የሕግ ዕውቅና እንዲያገኙ፣ እንዲበረታቱና እንዲስፉፉ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

መንግስት በፍትሕ ትራንስፎርሜሽን እቅዱ የማሕበረሰብ ፍትሕ ተቋማት እንዲስፋፉ በማድረግ እውቅና እየሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

ባሕላዊ የግጭት አፈታት ሥርዓት የፍትሕ ተደራሽነትን እያሳደገ መሆኑን አንስተው÷ በዚህም በማሕበረሰቡ መካከል የሚከሰቱ ግጭቶች እየተፈቱበት መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በቀጣይ ባሕላዊ የግጭት አፈታት ሥርዓቶችን ማጠናከር የሚያስችሉ ሥራዎች በትኩረት ይሰራሉ ማለታቸውንም ኢዜአ ነው የዘገበው፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!