አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ሁሉም ዜጎች በእኩል የሚስተናገዱበት አካታች ሥርዓት ነው አሉ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምጸሀይ ጳውሎስ።
የ10ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ፎረም ማጠቃለያ መርሐ ግብር የአፍሪካ ሕብረት፣ የአባል ሀገራት የስራ ኃላፊዎችና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ተካሂዷል።
ዓለምጸሀይ ጳውሎስ በዚህ ወቅት ፥ ኢትዮጵያ የሕዝብ አገልግሎቶችን ለማሳለጥ ያከናወነቻቸውን ተግባራት በተሞክሮነት ስታጋራ ክብር ይሰማናል ብለዋል።
የዘንድሮው የአፍሪካ ሕብረት የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ፎረም የተሰጠው መሪ ሃሳብ የተቋማትን የጋራ ርዕይ እውን ለማድረግ ትልቅ ምዕራፍ መሆኑን አንስተዋል።
በአፍሪካ መዲና አዲስ አበባ የዓድዋ ድል መታሰቢያ፣ የብሔራዊ ቤተ መንግስት ዕድሳት፣ የሳይንስ ሙዚዬም ግንባታ፣ የከተሞች የኮሪደርና የቱሪዝም ልማት ፕሮጀክቶች እየተሳለጡ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
የመሶብ አንድ ማዕከል የሕዝብን የአገልግሎት ፍላጎት ያማከለና ሁሉም የዜጎችን በቴክኖሎጂ የተጋዘ፣ በአክብሮትና በኃላፊነት መንፈስ የሚገለገሉበት መሆኑን አስገንዝበዋል።
ኢትዮጵያ የተሟላ ማዕድ በሚወክለው የመሶብ አገልግሎት በሁሉም አካባቢዎች በማስፋት በዘመናዊ አገልግሎት የጋራ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ እየሰራች እንደምትገኝ መጥቀሳቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የፎረሙ ተሳታፊዎች የመዲናዋ ጉብኝትም የአፍሪካ ህዝባዊ ተቋማት በአንድ ማዕከል ፍትሕዊና ዘመናዊ አገልግሎትን ለመሻሻል የተደረጉ ማሳያዎች መሆናቸውን ተናግረዋል።
የአፍሪካ የህዝብ አገልግሎት ቀን መካሄዱም በፍትሕዊነት፣ በዲጂታል ሥርዓት እንዲሁም ብቃት ባላቸው ሰዎች የሚመሩ ስኬታማ ተቋማትን ለመፍጠር ጉልህ ፋይዳ እንደሚኖረው ነው ያነሱት።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!