አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በወላይታ ሶዶ ከተማ በዛሬው ዕለት በደረሰው የትራፊክ አደጋ የሦስት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡
የሶዶ ከተማ ፖሊስ ዋና አዛዥ ምክትል ኮማንደር ሀብታሙ አሰፋ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንደገለጹት÷ በወላይታ ሶዶ ከተማ የፍሳሽ ማስወገጃ ተሽከርካሪ ባደረሰው አደጋ እስካሁን የ3 ሰዎች ሕይወት አልፏል።
በአደጋው በሦስት ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱንና ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል አንደኛው በአስጊ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በአደጋው ህይወታቸውን ያጡት ሦስቱም ወንዶች ሲሆኑ÷ ሁለቱ በመንገድ ላይ የነበሩ የመኪና ረዳቶችና አንድ የሊስትሮ ባለሙያ መሆኑን ነው የገለጹት።
ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችም ወደ ሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታልና ኦቶና ማስተማሪያ ሆስፒታል ለህክምና መወሰዳቸውን ጠቁመዋል።
የአደጋው መንስኤ በጉዞ ላይ የነበረ ፍሳሽ ማስወገጃ ተሽከርካሪ ባጋጠመው የቴክኒክ ችግር ፍሬን ያለመስራት ችግር በማጋጠሙ እንደሆነም አንስተዋል።
በዚህም ስድስት ተሽከርካሪዎችን በመግጨት ከባድ የንብረት አደጋ መድረሱንም ነው የተናገሩት።
በማስተዋል አሰፋ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!