አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የመከላከያ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታልን አገልግሎት አሰጣጥ ለማዘመን እየተሰራ ነው አሉ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ።
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የመከላከያ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና አሰጣጥ ሂደቱን በመመልከት የሆስፒታሉን የእንግዳ ማረፊያ መርቀው ከፍተዋል።
የእንግዳ ማረፊያው ሁሉንም ዓይነት የእንግዳ ማረፊያ መስፈርት ያሟላ 26 የመኝታ ክፍሎች አሉት።
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ሆስፒታሉ በህክምና መሣሪያዎች ቴክኖሎጂና በሙያተኛ ዘመናዊነትን በተከተለ አግባብ ዘምኖ የሪፈራል ሆስፒታል መሆን እንዲችል መከላከያ ከፍተኛ ገንዘብ ወጪ ማድረጉን አንስተዋል።
ሪፈራል ሆስፒታሉ ወደ ውጪ የሚሄዱ ታካሚዎች በሀገር ውስጥ እንዲታከሙ በሚደረጉ ጥረቶች ትልቅ ተስፋ ሰጪ ሆኗልም ነው ያሉት፡፡
ለዚህም የ86 የሠራዊት አባላት የዳሌ አጥንት ቅየራ ሥራ በውጤት መሳካት ዋናው ማሳያ እንደሆነ ማንሳታቸውን የመከላከያ ሠራዊት ኦንላይን ሚዲያ ለፋና ዲጂታል ገልጿል።
በመላኩ ገድፍ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!