የሀገር ውስጥ ዜና

ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ ጽዱ ሀገርን ለትውልድ ለማስተላለፍ እየተሰራ ነው

By Melaku Gedif

June 25, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሁለተኛው ዙር ክልል ዓቀፍ የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል።

የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሌሊሴ ነሜ (ኢ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ ጽዱ ኢትዮጵያን ባህል ማድረግ ከሁሉም ዜጋ የሚጠበቅ ተግባር ነው፡፡

የአካባቢ ብክለት የሚያደርሰውን ሁለንተናዊ ጉዳት ለማስቀረት በአንደኛው ምዕራፍ በተከናወኑ ተግባራት ዘርፈ ብዙ ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል ብለዋል፡፡

በንቅናቄው የፕላስቲክ፣ አፈር፣ ውሃ፣ የድምፅ እና የአየር ብክለቶችን በመከላከል ጽዱ ኢትዮጵያን ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚራሰራ አስረድተዋል፡፡

ለተግባራቱ ውጤታማነትም ሁሉንም ሕብረተሰብ ባሳተፈ መልኩ በትብብር መስራት ይገባል ነው ያሉት፡፡

የክልሉ ደን፣ አካባቢ ጥበቃና ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብርሃም መጫ በበኩላቸው ÷የአካባቢ ብክለት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ የሚያሳድረው አሉታዊ ተፅዕኖው ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

ሕብረተሰቡን ከተላላፊና ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች ለመጠበቅም አካባቢን ጽዱ፣ ምቹና ለኑሮ ተስማሚ ማድረግ እንደሚገባ ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡

በወንድማገኝ ጸጋዬ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!