አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ከመንግስት ጋር ተቀራርበው መምከራቸው የጋራ ትርክትን በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ይኖረዋል አሉ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ምሁራን።
ውይይቱ ሀገራዊ የልማት አጀንዳዎችን የመፈጸም አቅም በማስረጃ በማስደገፍ ለማቅረብ የአሰራር ምቹነትን ለሚዲያዎች እንደሚፈጥርም ምሁራኑ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጠቅሰዋል፡፡
በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን መምህር ደህናሰው ሽመልስ ውይይቱ በሚዲያዎች ያለው ጥንካሬና ተግዳሮት የተለየበት ነው ብለዋል፡፡
መንግስት ሙያዊ ሥነ ምግባርን ተከትለው ለሚሰሩ ሚዲያዎች ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኝነት ማሳየቱንም አድንቀዋል፡፡
በወልድያ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠንነትና ኮሙኒኬሽን መምህሩ ሀብታሙ ሙሉጌታ በበኩላቸው÷ ውይይቱ የሀገር ጥቅምና የሚዲያ ነጻነትን በተንተራሰ መልኩ ለመዘገብ ይበልጥ ግልጽነት የሰጠ ነው ብለዋል፡፡
ውይይቱ ተቀራራቢ ሀገራዊ ትርክት ለመፍጠር የጎላ ሚና እንዳለውም ነው የጠቆሙት።
በእዮናዳብ አንዱዓለም
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!