ስፓርት

ኦሮሚያ ክልል የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች አጠቃላይ አሸናፊ ሆነ

By Adimasu Aragawu

June 26, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ26 የስፖርት አይነቶች ሲካሄድ የቆየው 6ኛው መላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ውድድር በኦሮሚያ ክልል አሸናፊነት ተጠናቅቋል።

በውድድሩ ከ5 ሺህ በላይ ስፖርተኞች የተሳተፉ ሲሆን÷ በወንዶች የእግር ኳስ የፍፃሜ ጨዋታ ኦሮሚያ ክልል ደቡብ ኢትዮጵያን 2 ለ 1 በማሸነፍ የወርቅ ሜዳሊያ እና የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።

በተመሳሳይ የሴቶች እግር ኳስ ኦሮሚያ ደቡብ ኢትዮጵያን 1 ለ 0 በመርታት የወርቅ ሜዳሊያ እና የዋንጫ ተሸልሟል።

ከሰኔ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በጅማ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የመላ ኢትዮጵያ ሻምፒዮና ዛሬ ፍፃሜውን ሲያገኝ ኦሮሚያ ክልል የአጠቃላይ አሸናፊ ሆኗል።

በ19 የስፖርት ዓይነቶች 239 ሜዳሊያዎችን የሰበሰበው ኦሮሚያ ክልል 1ኛ ደረጃን ይዞ ሲያጠናቅቅ÷ አዲስ አበባ ከተማ በ216 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ሁለተኛ እንዲሁም አማራ ክልል 141 ሜዳሊያዎችን በማግኘት 3ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቅቀዋል።

በውድድሩ ኦሮሚያን ተከትሎ በአጠቃላይ ውድድር 2ኛ ደረጃን ይዞ የጨረሰው አዲስ አበባ ከተማ የፀባይ ዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።

በዳንኤል እንዳለ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!