የሀገር ውስጥ ዜና

ደቡብ ኮሪያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ወዳጅነት ወደላቀ የኢኮኖሚ ግንኙነት ማሳደግ ትሻለች

By Adimasu Aragawu

June 26, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ደቡብ ኮሪያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ዘመን ተሻጋሪ ወዳጅነት ወደላቀ የኢንቨስትመንት እና ኢኮኖሚ ግንኙነት ማሳደግ ትፈልጋለች አሉ የደቡብ ኮሪያ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ጆ ሆ ያንግ፡፡

የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ከፍተኛ የደቡብ ኮሪያ ልዑካን ቡድን አባላትን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

ምክትል አፈ ጉባኤ ጆ ሆ ያንግ ውይይቱ ተከትሎ በሰጡት አስተያየት፥ ኢትዮጵያ ለደቡብ ኮሪያ ሰላም ለከፈለችው መስዋዕትነት ያላቸውን ክብር ለፕሬዚዳንት ታዬ መግለፃቸውን ተናግረዋል፡፡

ደቡብ ኮሪያ በኢንቨስትመንት እና ልማት ዘርፎች ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር መስራት እንደምትፈልግም አብራርተዋል፡፡

ለዚህም በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ቁርጠኝነት መኖሩን ከፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ስላሴ ማረጋገጫ ማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡

የልዑክ ቡድኑን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው ያነጋገሩት ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ÷ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ እንዲሸጋገር በኢትዮጵያ በኩል ፍላጎት መኖሩን አመልከተዋል፡፡

የደቡብ ኮሪያ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ያላቸው ኢንቨስትመንት እንዲጠናከር መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍም ያደርጋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የደቡብ ኮሪያ የምክር ቤት አባላትን ያካተተው ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረገ ይገኛል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!