የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ የተገነቡ 107 የህዝብ ንጽሕና መጠበቂያ ቤቶች አገልግሎት ጀመሩ

By Abiy Getahun

June 27, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር ልማቱን ተከትሎ የተገነቡ 107 የህዝብ ንጽሕና መጠበቂያ ቤቶች አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ የህዝብ መጸዳጃ ቤቶች አስተዳደር ቡድን መሪ ጸዳሉ መሰለው እንዳሉት፤ የኮሪደር ልማቱ ለጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል።

የኮሪደር ልማቱን ተከትሎ የተገነቡ 107 የህዝብ ንጽህና መጠበቂያ ቤቶች አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን ገልጸው፤ በቅርቡ በርካታ የንጽሕና መጠበቂያ ቤቶች ወደ አገልግሎት እንደሚገቡም ጠቁመዋል።

በተጨማሪም የኮሪደር ልማት በሌለባቸው አካባቢዎች ላይ የጤና ሚኒስቴር ከዓለም ባንክ ጋር በመተባበር የህዝብ ንጽሕና መጠበቂያ ቤቶችን እየገነባ ነው ብለዋል።

በቀጣዩ ዓመትም በቢሮው በኩል 100 የህዝብ የንጽሕና መጠበቂያ ቤቶች እንደሚገነቡ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል።

ማህበረሰቡ በህዝብ ንጽህ መጠበቂያ ቤቶች መጠቀም እንዲችል በተሰራው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ መንገድ ላይ የመጸዳዳት ድርጊት መቀነሱን አንስተዋል።

በመዲናዋ ከዚህ ቀደም በተገነቡ የህዝብ ንጽሕና መጠበቂያ ቤቶች 250 እና በኮሪደር ልማቱ ደግሞ 57 ማህበራት ተደራጅተው እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በመሳፍንት እያዩ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!