አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሌስተር ሲቲ ከአሰልጣኝ ሩድ ቫን ኒስትሮይ ጋር መለያየቱን ይፋ አድርጓል፡፡
የ48 ዓመቱ የቀድሞ የማንቼስተር ዩናይትድ ተጫዋች ባለፈው የውድድር ዓመት ሌስተር ሲቲን ከተረከበ በኋላ ካደረጋቸው 27 ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው 5ቱን ብቻ ነው፡፡
ቀበሮዎቹ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ በመጡበት ዓመት ወደ ሻምፒዮንሺፕ መውረዳቸው የሚታወስ ሲሆን ፥ ከአሰልጣኝ ሩድ ቫን ኒስትሮይ ጋር እንደሚለያዩ በስፋት ሲነገር ቆይቷል፡፡
ሌስተር ሲቲ ዛሬ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ እንዳለው÷ ከአሰልጣኝ ሩድ ቫን ኒስትሮይ ጋር በስምምነት ተለያይተዋል፡፡
ሩድ ቫን ኒስትሮይ ለክለቡ ስኬታማ ጊዜን በመመኘት፥ ለተጫዋቾችና በኪንግ ፓወር ቆይታው አብረውት ለሰሩት የቡድኑ አባላት ምስጋና አቅርቧል፡፡
በኃይለማርያም ተገኝ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!