የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ በአስደናቂ የሕዳሴ ጉዞ ላይ ናት – የናይጄሪያ ም/ፕሬዚዳንት ካሺም ሼቲማ

By Melaku Gedif

June 27, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በአስደናቂ የሕዳሴ ጉዞ ላይ ትገኛለች አሉ የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዚዳንት ካሺም ሼቲማ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከናይጄሪያ ም/ፕሬዚዳንት ካሺም ሼቲማ ጋር ቁልፍ በሆኑ የሁለትዮሽ እና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸው ይታወቃል።

ምክትል ፕሬዚዳንቱ የኢትዮጵያን አስደናቂ ቅርሶችና ታሪኳን አጉልቶ በሚያሳይ መልኩ ታድሶ ለዕይታ ክፍት የሆነውን ብሔራዊ ቤተ መንግሥትንም ጎብኝተዋል።

ጉብኝታቸውን በተመለከተ በይፋዊ የክብር መዝገብ ላይ ባሰፈሩት የማስታወሻ መልዕክት ብሔራዊ ቤተ መንግሥቱ ህያው ታሪክ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቅኝ ያልተገዛች ብቸኛዋ ሀገር መሆኗን ያወሱት ምክትል ፕሬዚዳንቱ ፥ በአስደናቂ የሕዳሴ ጉዞ ላይ ትገኛለች ነው ያሉት።

በኢትዮጵያ ድንቅ የታሪክ ጸጋና ታላቅ ሀገርነት ኩራት እንደተሰማቸው መግለጻቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

YouTube (http://www.youtube.com/@fanamediacorporation)