አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሐረማያ እና ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች ወደ ፈተና ማዕከላት መግባት ጀምረዋል፡፡
ተፈታኝ ተማሪዎቹ ወደ ማዕከላቱ ሲገቡ የዩኒቨርስቲዎቹ ከፍተኛ አመራሮችና የአካባቢው ማህበረሰብ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ 7 ሺህ 29 ተማሪዎች በወረቀት የሚፈተኑ ሲሆን፤ 592 ተማሪዎች ደግሞ በበይነ መረብ ፈተናውን እንደሚወስዱ የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት መንግስቱ ኡርጌ (ፕ/ር) ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ገልፀዋል።
በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ 1 ሺህ 72 ተማሪዎችም ወደ ዩኒቨርሲቲው እየገቡ መሆናቸውን የዩኒቨርሲቲው ሬጂስትራር ጉዳዮች ዳይሬክተር ጂብሪል አልብዱልቃድር (ዶ/ር) ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን አብራርተዋል፡፡
በወረቀትና በበይነ መረብ የሚፈተኑት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተናቸውን ከኩረጃ በፀዳ መልኩ ማከናወን እንዲችሉ ከወዲሁ አስፈላጊው ጥንቃቄ እየተደረገ እንደሆነ አመላክተዋል።
የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል፡፡
በተሾመ ኃይሉ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!