የሀገር ውስጥ ዜና

በጥገና ምክንያት ዛሬ ሌሊት በተወሰኑ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ይቋረጣል

By Abiy Getahun

June 27, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ ሴንተር ወይም በሜክሲኮ ማከፋፈያ ትራንስፎርመር ላይ በሚከናወን አስቸኳይ የጥገና ሥራ ምክንያት ዛሬ ሌሊት በተወሰኑ አካባቢዎች ኃይል ይቋረጣል አለ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፡፡

የተቋሙ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንደገለፁት፤ ዛሬ ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ከሌሊቱ 6 ሰዓት ጀምሮ በሚከናወነው የጥገና ሥራ ምክንያት ከማከፋፈያ ጣቢያው ኃይል የሚያገኙ አካባቢዎች ኃይል ይቋረጥባቸዋል።

የማከፋፈያ ጣቢያዎች ላይ ልዩ ጥገና እንደሚደረግ ገልጸው፤ ከጥገናዎቹ መካከል አንደኛው ዛሬ ሌሊት የሚደረገው ጥገና አንዱ መሆኑን ተናግረዋል።

አስቸኳይ ጥገና የሚደረገው ትራንስፎርመሮች ጭነት እንዳይበዛባቸው ታሳቢ ተደርጎ እንደሆነ ጠቅሰው፤ ጥገናው የአገልግሎት አሰጣጡን የተሻለ ለማድረግ በማሰብ ነው ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት የኃይል አጠቃቀም እያደገ በመምጣቱ የትራንስፎርመሮችን ደህንነት የማረጋገጥ ሥራ አስቀድሞ መሰራት እንዳለበት አንስተዋል።

በመሆኑም በዛሬው ሌሊት ልዩ ጥገና ከሚካሄድባቸው መስመሮች ኃይል የሚያገኙ አካባቢዎች ኃይል እንደሚቋረጥባቸው ጠቁመዋል።

በመሆኑም ሜክሲኮ፣ ቄራ፣ ገነት ሆቴል፣ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አካባቢ፣ መስቀል ፍላወር፣ ወሎ ሰፈር፣ መስቀል አደባባይ፣ ባምቢስ እና አካባቢው እንደሚገኙበት አስረድተዋል፡፡

የጥገና ሥራው እስከሚጠናቀቅ ድረስም በተጠቀሱት አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ መልዕክት መተላለፉን ገልጸዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!