የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ሁሉም እንዲሳተፍ ጥሪ አቀረቡ

By Abiy Getahun

June 27, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ማንሰራራት ማሳያ በሆነው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል ይካሄዳል ብለዋል።

የአረንጓዴ ዐሻራ እጅግ ዘርፈ ብዙ ትርፋቶችን ያስገኘ ሥራ መሆኑን ጠቅሰው፤ በዚህ ዓመት ከሚተከለው ችግኝ ጋር ወደ 47 ነጥብ 5 ቢሊየን ገደማ ይደርሳል ብለዋል፡፡

በዚህም በሚቀጥለው ዓመት ከሚተከለው ጋር ሲደመር 54 ቢሊየን ሊደርስ እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

በዚህ መርሃ ግብር ያመናችሁ፣ የተሳተፋችሁ እጆቻችሁ ጭቃ የነካ፤ የተከላችሁ፤ የተንከባከባችሁ ኢትዮጵያውያን፣ በኢትዮጵያ የምትገኙ ዲፕሎማቶች፣ ይህንን ህልም የደገፋችሁ የየትኛውም ሀገር ዜጎች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ ያለን ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከነገ ጀምሮ በየዕለቱ የኢትዮጵያ ማንሰራራት ማሳያ በሆነው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ሁሉም የህብረተሰብ ክፍልና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ እንዲሳተፍ ጥሪዬን አቀርባለሁ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!