አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ ፈተና ማዕከላት እየገቡ ነው።
ተማሪዎቹ ከሰኔ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የሚሰጠውን ፈተና ለመውሰድ ወደ ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ፣ ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ሚዛን አማን እና ቴፒ ካምፓሶች ፣ ወላይታ ዩኒቨርሲቲ ታርጫ ካምፓስ ወደ ተዘጋጁ ማዕከላት እየገቡ እንደሆነ የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ የሺዋስ ዓለሙ ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል።
በክልሉ የግል ተፈታኝ የሆኑ ከ3 ሺህ በላይ የሆኑ ተማሪዎችን ጨምሮ 19 ሺህ 127 ተማሪዎች ለ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና መዘጋጀታቸውን የገለጹት አቶ የሺዋስ፤ ተማሪዎች የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ የማዘጋጀት ሥራዎች መሰራታቸውን አስታውሰዋል።
በዚህም ፈተናው በኦንላይንና በወረቀት የሚሰጥ በመሆኑ ለተማሪዎች አዲስ እንዳይሆን የተግባር ልምምዶች መደረጋቸውንም ጠቅሰዋል።
ተማሪዎቹ ወደ ተለያዩ አካባቢዎች በመሄድ የሚፈተኑ በመሆኑ ከመደበኛ ትምህርታቸው ጎን ለጎን የሥነ ልቦና ዝግጅት ሲያደርጉ ቆይተዋል ብለዋል።
የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ማሳወቁ ይታወሳል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!