ጤና

ከ100 በላይ የኤምፖክስ ለይቶ ማቆያና ማከሚያ ማዕከላት ተዘጋጅተዋል

By Abiy Getahun

June 28, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በመላው ኢትዮጵያ ከ100 በላይ የኤምፖክስ ለይቶ ማቆያና ማከሚያ ማዕከላት ተዘጋጅተዋል አለ፡፡

በኢንስቲትዩቱ የኤምፖክስ ቅኝት አስተባባሪ ሚኪያስ አላዩ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንደገለፁት፤ በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች በሽታውን መቆጣጠር የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ተሰርተዋል።

የለይቶ ማቆያና ማከሚያ ማዕከላትም ቀድመው ዝግጁ መደረጋቸው በሽታውን በቀላሉ ለመግታት ያስቸላል ነው ያሉት።

በተጨማሪም ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ ቡድን በማቋቋም የኤምፖክስ በሽታ እንዳይስፋፋ ሰፊ የቅኝት ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

ከበሽታው ጋር ለተያያዙ መረጃዎችና ጥቆማ ለማድረግ ደግሞ 8335 እና 952 ነፃ የስልክ መስመሮችን መጠቀም እንደሚቻል አቶ ሚኪያስ አላዩ አመላክተዋል፡፡

የኤምፖክስ በሽታ በኢትዮጵያ መገኘቱ ከተገለጸበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ትናንትናው ዕለት ድረስ 24 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው በላቦራቶሪ በተደረገ ምርመራ ተረጋግጧል።

በዙፋን ካሳሁን

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!