አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ለሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ከይዞታቸው ለተነሱ 432 አርሶአደሮች ምትክ ቦታ አስረከበ።
የቤንች ሸኮ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትን እንዳሉት፤ ለፕሮጀክቱ ግንባታ የሚነሱ አርሶ አደሮች አብሮነታቸውና ማህበራዊ መስተጋብራቸው እንዳይፈርስ ጥረት ተደርጓል።
በዚህም ከአካባቢያቸው ሳይርቁ ምትክ ቦታ እንዲያገኙ መደረጉን ገልጸው፤ ከመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ በተጨማሪ ከ1 ሺ 900 በላይ ለሚሆኑ አርሶ አደሮች የእርሻ ቦታ ተዘጋጅቷል ነው ያሉት።
እስካሁን ከ500 በላይ የሚሆኑ አርሶ አደሮች የእርሻ ቦታ መረከባቸውንም አስረድተዋል።
ለሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ካሳ ክፍያ ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ያስፈልጋል ያሉት አቶ ሀብታሙ፤ የዞኑ አስተዳደር እስካሁን ከ160 ሚሊየን ብር በላይ የካሳ ክፍያ መፈጸሙን ተናግረዋል።
ለልማቱ ከቦታቸው የተነሱ አርሶ አደሮች በፕሮጀክቱ ደስተኛ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ በሚሰፍሩባቸው አካባቢዎች አስፈላጊ መሠረተ ልማት እንዲሟላ ጠይቀዋል።
የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሰሎሞን ሎዊ (ኢ/ር) በአጭር ጊዜ ውስጥ መሰረተ ልማት የሚሟላ መሆኑን አረጋግጠዋል።
በተስፋዬ ምሬሳ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!