አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በቀጣዮቹ የ2018 እና 2019 ምርት ዘመን የምርጥ ዘር ፍላጎትን ለማሟላት ከወዲሁ እየሰራሁ ነው አለ፡፡
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አብዮት መብራቴ (ዶ/ር) እንደገለፁት፤ ኢንስቲትዩቱ ምርታማነት እንዲጨምር አዳዲስ ምርጥ ዘሮችን የማዘጋጀት፣ የማስተዋወቅ እና የማላመድ ስራ ያከናውናል፡፡
ባለፉት ዓመታት የምርጥ ዘር አቅርቦት ከአርሶ አደሩ ፍላጎት ጋር ባለመጣጣሙ መስተጓጐል ተከስቶ እንደነበር አስታውሰው፤ ችግሩን ለመፍታት እየተሰራ እንደሆነ አብራርተዋል።
በዚህም በክልሉ ባሉ የምርምር ማዕከላት የየአካባቢውን ስነ ምህዳር መሠረት አድርገው የመነሻ ዘር ብዜት ሥራ በማከናወን ላይ እንደሚገኙ አስረድተዋል፡፡
በአርባምንጭ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት አማካኝነት በ10 ሄክታር ማሳ ላይ እስከ 140 ኩንታል የሚጠበቅና ምርታማነቱ ከሌሎች የተሻለ መሆኑ የተረጋገጠ የበቆሎ ዘር እየተመረተ ይገኛል ብለዋል።
የማዕከሉ ዋና ተልዕኮ የተለያዩ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅ፣ በማላመድ እና በማስተዋወቅ ረገድ ውጤታማ ለመሆን ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
በአርሶ አደር ዘንድ ተቀባይነት ያገኙ ቴክኖሎጂዎችን በማባዛትና በማስፋፋት ለተለያዩ አካባቢዎች አገልግሎት እየተሰጠ ነው ያሉት ደግሞ የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ቱማ አየለ (ረ/ፕ) ናቸው።
ምርታማነትን ለመጨመር ጥራቱን የጠበቀ ምርጥ ዘር አስፈላጊ በመሆኑ የምርጥ ዘር አቅርቦት ችግር ለመፍታት በቁርጠኝነት ይሰራል ነው ያሉት።
በመለሰ ታደለ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!