የሀገር ውስጥ ዜና

አንድነታችንን አጠናክረን ማህበረሰቡን በባህል እና በልማት ተደራሽ ማድረግ ይገባል – እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

By Abiy Getahun

June 28, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የጉራጌ ህዝብ ውስጣዊ አንድነቱን በማጠናከር ከሌሎች ወንድም እና እህት ህዝቦች ጋር ያለውን ትስስር ማጠናከር ይገባዋል አሉ፡፡

የጉራጌና ምስራቅ ጉራጌ ዞኖች በጋራ ያዘጋጁት የጉራጌ ህዝብ ባህል፣ ቋንቋና ታሪክ ሲምፖዚየም በተለያዩ ዝግጅቶች በወልቂጤ ከተማ እየተከበረ ነው።

ሲምፖዚየሙን የከፈቱት እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) እንዳሉት፤ የጉራጌ ህዝብ ባህሉን ለማስተሳሰር ሲሰራ ቆይቷል።

የዚህ አይነቱ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበው፤ የጉራጌ ህዝብ በትጋት በብልሃትና በታታሪነት የማይታማ ህዝብ መሆኑ ለኢትዮጵያም ብዝሃነት የራሱ የሆነ ድርሻ አለው ብለዋል።

ህዝቡ በሰላሙ የማይደራደር እና ባህሉን በመጠበቅ ከትውልድ ወደ ትውልድ ያሻገረ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ሲምፖዚየሙ ወጣቶች ከባህላቸውና ከቋንቋ ጋር ትስስር እንዲፈጥሩ እድል የሚፈጥር መሆኑን በመጥቀስ፤ ቋንቋውን ለማሳደግና ለማልማት መስራት ይኖርብናል ሲሉ ገልፀዋል::

አንድነታችንን አጠናክረን ማህበረሰቡን በባህል እና በልማት ተደራሽ በማድረግ የሚጠበቅብንን መስራት ይጠበቅብናል ነው ያሉት።

ሲምፖዚየሙ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የጉራጌ ተወላጆች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል::

በዘቢብ ተክላይ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!