አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ሁሉም ዜጋ ሀገር ለመለወጥ በባለቤትነት የሚሳተፍበት የትውልድ አሻራ ነው አሉ፡፡
በዛሬው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዝዳንት ካሺም ሼቲማን እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻ ልማት የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ተካሂዷል።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በወቅቱ እንደገለጹት፤ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከሀገራዊ ኢኮኖሚያዊ ልማት ጋር የተሳሰረ ነው።
የአየር ንብረት ለውጥ በምርታማነት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንዳለው ጠቁመው፤ ከዚህ አኳያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አካባቢን ከመለወጥ ባሻገር ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ማንሰራራት ትልቅ ሚና እንዳለው አብራርተዋል።
የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ሁሉም ዜጋ ሀገር ለመለወጥ በባለቤትነት የሚሳተፍበት የትውልድ ስራ መሆኑንም ተናግረዋል።
ሁሉም ዜጋ እጅ ለእጅ ተያይዞ በጋራ ከሰራ ኢትዮጵያ በአጭር ጊዜ እንደምትለወጥ ጠቁመው፤ የተጀመሩ ስራዎችን በትብብር ማስቀጠል ይገባል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
“በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ሃሳብ በሚካሄደው በዘንድሮው አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በሀገር አቀፍ ደረጃ 7 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኞች ይተከላሉ።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!