ዓለምአቀፋዊ ዜና

ጆርጅ ኤሎምቢ የአፍሪኤግዚም ባንክ ፕሬዚዳንት ሆኑ ‎

By Abiy Getahun

June 28, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የካሜሩን ዜግነት ያላቸው ጆርጅ ኤሎምቢ የአፍሪካ ኤክስፖርት ኢምፖርት (አፍሪኤግዚም) ባንክ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ። ‎ ‎ተመራጩ ፕሬዚዳንት የባንኩን የዳይሬክተሮች ቦርድ በሊቀመንበርነት ይመራሉ። ‎ ‎ኢሎምቢ የተመረጡት ባንኩን ላለፉት 10 ዓመታት በፕሬዚዳንትና የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር የነበሩትን ቤኔዲክት ኦራማህ (ፕ/ር) በመተካት ነው። ‎ ‎በባንኩ ባለድርሸዎች ጠቅላላ ጉባዔ የተመረጡት ኤሎምቢ ባንኩን በምክትል ፕሬዚዳንትነት እና በተለያዩ ደረጃዎች ላለፉት 20 ዓመታት ማገልገላቸው ተገልጿል። ‎ ኤሎምቢ ከተመሠረተ 32 ዓመታት ያስቆጠረውን ባንክ ለመምራት አራተኛው ፕሬዚዳንት ሆነዋል ሲል የባንኩ መረጃ አመልክቷል።

የባንኩ ሦሰተኛ ፕሬዚዳንት ሆነው ያገለገሉት ቤኔዲክት ኦራማህ (ፕ/ር) ባንኩን ወደላቀ ደረጃ እንዲሸጋገር አድርገዋል ተብሏል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!