ቴክ

”ለችግር ፈች የምርምርና ኢኖቬሽን ሥራዎች አስፈላጊው ድጋፍ እየተደረገ ነው” በለጠ ሞላ (ዶ/ር)

By Abiy Getahun

June 28, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ችግር ፈች የምርምርና ኢኖቬሽን ሥራዎችን ለማጠናከር የዘርፉን ምህዳር ማስፋት ይገባል አሉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር)።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያዘጋጀው ሀገራዊ የምርምርና ኢኖቬሽ ወርክ ሾፕና ሲምፖዚዬም በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሰው ኃብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር)፣ ተመራማሪዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ ላይ በለጠ ሞላ (ዶ/ር) እንዳሉት፥ የምርምር እና የኢኖቬሸን ሥራዎች ችግር ፈቺ እንዲሆኑ በትኩረት እየተሰራ ነው።

የፈጠራ ሥራዎች ለአንድ ሀገር እድገት መሰረት ናቸው ያሉት ሚኒስትሩ፥ ለዚህም ዘመኑን የዋጁ የምርምር ሥራዎች ያስፈልጋሉ ብለዋል።

ወጣቶች በፈጠራና ምርምር ሥራዎች እንዲሳተፉ ትኩረት መደረጉን በመጥቀስ፥ ለውጤታማነቱም አስቻይና የጎለበተ ምህዳር መፍጠር እንደሚገባ አንስተዋል።

የግል ዘርፉ በስታርታፕ እና ሌሎች የፈጠራ ሥራዎች እንዲሳተፍ የዘርፉ ምህዳር እንዲሰፋ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፤ ተቋማት ለችግር ፈቺ የምርምርና ኢኖቬሽን ሥራዎች መጠናከር አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉም ጠይቀዋል።

ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር በበኩላቸው፥ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ለተጀመረው ጥረት መሳካት የምርምና ኢኖቬሽን ሥራዎች ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል።

ዘርፉን ይበልጥ ለማዘመንና አስቻይ ሁኔታ ለመፍጠርም ፖሊሲና ስትራቴጂዎችን በማዘጋጀት መስራት ይገባል ነው ያሉት።

ለችግር ፈች የምርምርና ኢኖቬሽን ሥራዎች አስፈላጊውን የፋይናንስ ድጋፍና ክትትል ማድረግ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ቋሚ ኮሚቴው ለዘርፍ መጠናከርና መጎልበት የሚያደርገውን ክትትል እንደሚያጠናክርም አረጋግጠዋል።

በመርሐ ግብሩ በተለያዩ ዘርፎች የተከናወኑ የምርምርና የኢኖቬሽን ሥራዎች ለዕይታ ቀርበዋል።

በመላኩ ገድፍ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!