አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ የ7ኛው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ማስጀመሪያ “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ ይገኛል።
በመርሐ ግብሩ ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባስተላፉት መልዕክት÷ በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ ባለፉት ስድስት ዓመታት 85 ሚሊየን ችግኞች መተከላቸውን ጠቁመዋል።
በዚህም የከተማዋ የደን ሽፋንም ከ2 ነጥብ 8 አሁን ላይ 22 በመቶ መድረስ መቻሉን ገልጸው÷ ኢትዮጵያ ችግኞችን በመትከል ተረጂነትን ታሪክ ለማድረግ እየሰራች ነው ብለዋል።
አዲስ አበባን ለመኖር ምቹና ጽዱ ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አንስተው÷ ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ የአረንጓዴ አሻራ ስራዎች ወንዞች ማንሰራራት መጀመራቸውንና በአፈርና ውሃ ጥበቃም ውጤቶች መታየት እንደጀመሩ መናገራቸውን የከተማ አስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ለፋና ዲጂታል ገልጿል።
በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ቡዜና አልቃድር፣ በብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሞገስ ባልቻ፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የኪነጥበብ ባለሙያዎች፣ የስፖርት ማህበረሰብ፣ የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች እና ሌሎችም ተገኝተዋል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ሐሳብ 7 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኞች እንደሚተከሉም ይጠበቃል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!