የሀገር ውስጥ ዜና

የአማራ ክልል የሽምግልና መማክርት ምስረታ ማብሰሪያ ገባኤ ተካሄደ

By Adimasu Aragawu

June 29, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ክልል የሽምግልና መማክርት ምስረታ የማብሰሪያ ገባኤ በባሕር ዳር ከተማ ተካሄደ።

በጉባኤው በአማራ ክልል ከሚገኙ 22 ዞኖች የተመረጡ የሀገር ሽማግሌዎች የተካተቱበት ክልላዊ የሽምግልና መማክርት ተመስርቷል።

የሽማግሌዎች መማክርት መመስረት ሀገር በቀል የሽምግልና ሥርዓቶች ለዘላቂ ሰላም ግንባታ ያላቸውን ዋስትና መሰረት በማድረግ ባህላዊ የሰላም እሴቶችን ለማዳበር የሚኖረው አስተዋጽኦ የላቀ መሆኑ ተገልጿል።

የሽማግሌዎች መማክርት ጉባኤ ራሱን የቻለ መተዳደሪያ ደንብ ያለው ሆኖ በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የሚደገፍና በገለልተኝነት ለሀገር ሰላም የሚሠራ የባህል አደረጃጀት ነው።

በማብሰሪያ መርሐ ግብሩ ላይ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ ማኅበራዊ ጉዳዮች፣ ባህልና ስፖርት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወርቀሰሙ ማሞን ጨምሮ የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በደሳለኝ ቢራራ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!