የሀገር ውስጥ ዜና

የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና እየተሰጠ ነው

By Melaku Gedif

June 30, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና በሁሉም የመፈተኛ ማዕከላት መሰጠት ጀምሯል አለ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት፡፡

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ÷ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና በዛሬው ዕለት በኦንላይንና በወረቅት እየተሰጠ እንደሚገኝ ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና በተፈጥሮ ሳይንስና በማህበራዊ ሳይንስ በአጠቃላይ 608 ሺህ 588 ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ አንስተዋል፡፡

በአራት ዙር በሚሰጠው ፈተና 140 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች ፈተናውን በኦንላይን እንሚወሰዱ ነው የገለጹት፡፡

ተማሪዎች ለፈተና የተከለከሉ ነገሮችን መያዝ እንደሌለባቸው ያሳሰቡት (ዶ/ር) እሸቱ ÷ ፈተናውን ተረጋግተው መፈተን እንዳለባቸውም መክረዋል፡፡

ባለፉት ቀናት የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ መፈተኛ ማዕከላት ሲገቡ መቆየታቸውን አስታውሰዋል፡፡

የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የማጠናቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23 ጀምሮ እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል፡፡

በመላኩ ገድፍ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!