የሀገር ውስጥ ዜና

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአንድነት እና የሰላም ጉባኤ እየተካሄደ ነው

By Mikias Ayele

June 30, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሰላም፣ የአንድነት እና የልማት ጉባኤ በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ነው።

ጉባዔው “ጠንካራ ክልላዊ አንድነትና አብሮነት ለዘላቂ ሠላምና ብልጽግና” በሚል መሪ ሐሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አባይነህ አበራ ለፋና ዲጂታል እንደገለጹት÷ ጉባኤው በክልሉ የሚገኙ ከ32 በላይ ብሔርና ብሔረሰቦችን በሰላም እና በልማት ለማስተሳሰር ያለመ ነው፡፡

ጉባኤው በክልል እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ለማጠናከር እና ክልላዊ የጋራ ራዕይን ለማረጋገጥ ታስቦ እየተካሄደ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

በጉባኤው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፣ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ እና ሌሎች የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በሚኪያስ አየለ