የሀገር ውስጥ ዜና

ምቹ የመማሪያ ማዕከላትን በማዘጋጀት ረገድ ውጤታማ ሥራ ተከናውኗል – እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

By Adimasu Aragawu

June 30, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ለተማሪዎች ሰላማዊና ምቹ የመማሪያ ማዕከላትን በማዘጋጀት ረገድ ውጤታማ ሥራ ተከናውኗል አሉ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ባስጀመሩበት ወቅት እንዳሉት፤ በክልሉ የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል የቅድመ ዝግጅት ስራ ተግባራዊ ሲደረግ ቆይቷል።

የመምህራንን አቅም ማሳደግ ልዩ ትኩረት እንደተሰጠው አስታውሰው፤ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት እና በሞዴል ፈተናዎች በቂ ልምምድ እንዲያደርጉ መሰራቱን ተናግረዋል።

በክልሉ 35 ሺህ 246 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተናን እንደሚወስዱ ጠቅሰው፤ ለዘርፉ ከተሰጠው ልዩ ትኩረት አንጻር ከአምናው የተሻለ ውጤት ይመዘገባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል።

ለተማሪዎች ሰላማዊና ምቹ የመማሪያ ማዕከላትን በማዘጋጀት ረገድ ውጤታማ ሥራ ተከናውኗል ያሉት እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)፤ በክልሉ በዛሬው እለት ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች እንደየ ፍላጎታቸው በወረቀት እና በኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች የታገዘ ፈተና እየተሰጠ ነው ብለዋል።

በኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ለሚፈተኑ ተማሪዎች በሁሉም ማዕከላት አማራጭ የኃይል አቅርቦት እና የኢንተርኔት አገልግሎት ዝግጁ ማድረግ እንደተቻለም ተናግረዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!