አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከዓለም አቀፍ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ (IAEA) ዋና ዳይሬክተር ማሪያኖ ግሮሲ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ዛሬ ጠዋት በሬይስ ኦፍ ሆፕ ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ከመጡት የዓለም አቀፍ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ማሪያኖ ግሮሲ ጋር ተወያይተናል ብለዋል።
የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኃይል በኢትዮጵያ የሚያደርገው ድጋፍ በካንሰር ሕክምና ክብካቤ፣ የእንስሳት ጤና፣ የፀፀ ፍላይ ዝንብ ማጥፊያ፣ በኒውክሌር ኢንጂነሪንግ እና የቁጥጥር ማዕቀፎች ላይ ያተኮረ መሆኑን አንስተዋል፡፡
ምክክሩ በመካሄድ ላይ ባሉ ድጋፎች እና የወደፊት የትብብር እድሎች ላይ ያተኮረ እንደነበርም አመልክተዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporationFacebook www.facebook.com/fanabroadcastingTelegram t.me/fanatelevisionWebsite www.fanamc.comTikTok www.tiktok.com/@fana_televisionWhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainmentFacebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporateTikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainmentAmharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!