አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ያለውን እምቅ የተፈጥሮ ሃብት በመጠቀም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ መስራት ይገባል አሉ በም/ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ፡፡
አቶ አደም ፋራህ በወላይታ ዞን ሁምቦ ወረዳ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው በመጎብኘት የአረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡
በዚህ ወቅትም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተለያዩ ዘርፎች መልማት የሚችል እምቅ የተፈጥሮ ሃብት እንዳለው አውስተዋል፡፡
ይህን አቅም ወደ ተግባር በመቀየር የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በትኩረት መስራት ይገባል ነው ያሉት፡፡
በሁምቦ ከተማ የተከናወኑ የሌማት ትሩፋት ሥራዎች አበረታች መሆናቸውን ጠቁመው÷ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡
በአካባቢው ያለውን የእንስሳት ሃብት በሚገባ በመጠቀም ዘርፉ በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ያለውን ሚና ማሳደግ እንደሚገባ አንስተዋል፡፡
“በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ሃሳብ በተጀመረው የዘንድሮው አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የክልሉ ሕዝብ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
አቶ አደም ፋራህ በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው ክልል አቀፍ የሰላም፣ የልማትና የአንድነት ሕዝባዊ ጉባዔ የማጠቃለያ መድረክ ላይ በነገው ዕለት እንደሚታደሙ የክልሉ ኮሙኒኬሽን ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡
በመላኩ ገድፍ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!