የሀገር ውስጥ ዜና

ለ2018 ዓም የቀረበው ረቂቅ በጀት የማክሮ ኢኮኖሚ ዕድገትን ከማሻሻል አንፃር ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋል – አቶ አህመድ ሺዴ

By Adimasu Aragawu

July 01, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ለ2018 ዓም የቀረበው ረቂቅ በጀት አጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚ ዕድገትን ከማሻሻል አንፃር ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋል አሉ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ።

ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 41ኛ መደበኛ ስብሰባ በፌዴራል መንግስት የ2018 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት ዙሪያ እየተደረገ ባለው ውይይት ላይ ነው።

የገንዘብ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ ከአበዳሪ ሀገራት ጋር በሚደረገው የዕዳ ሽግሽግ ድርድር የ3 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር እፎይታ ለማግኘት እየተሰራ ነው፡፡

ከአበዳሪ ሀገራት ጋር በዕዳ ሽግሽግ የሚደረገውን ድርድር በማጠናከር በቅርቡ እንፈራረማለንም ነው ያሉት።

ምንም እንኳን የዕዳ ሽግሸግ ከአበዳሪ ሀገራት ብናገኝም የምንከፍለው የገንዘብ መጠን ግን ይጨምራል ያሉት አቶ አሕመድ÷ ክፍያውን ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ መክፈል እንጀምራለን ብለዋል።

ባለፉት ዓመታት በተሰሩ ስራዎች የኢኮኖሚ ዕድገቱ መሻሻል ማሳየቱን ገልጸው÷ ይህም ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ጋር የመጣ መሆኑን አንስተዋል።

ብዙ የልማት ጥያቄዎች ቢኖሩም የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን በማያዛባ መልኩ ስራዎችን መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በወንድማገኝ ፀጋዬ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!