የሀገር ውስጥ ዜና

በምክር ቤቱ የጸደቁ ፕሮጀክቶችን ለመጨረስ ወደ 1 ነጥብ 5 ትሪሊየን ብር ያስፈልጋል – አቶ አህመድ ሺዴ

By Adimasu Aragawu

July 01, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው በ2018 ረቂቅ በጀት ላይ ከምክር ቤቱ ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም የልማት ጥያቄዎች ብዙ በመሆናቸው ሁሉንም ጥያቄዎች ለመመለስ አቅም እንደሚጠይቅ አንስተው÷ በ2018 በጀት ዓመት አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ከመጀመር ይልቅ የተጀመሩትን ለማጠናቀቅ ትኩረት ተደርጓል ብለዋል።

አሁን ባለው ሁኔታ ምክር ቤቱ ያጸደቃቸውን ፕሮጀክቶች ለመጨረስ ወደ 1 ነጥብ 5 ትሪሊየን ብር ያስፈልጋልም ነው ያሉት።

በምክር ቤቱ ጸድቀው ጨረታ ያልወጣላቸው ፕሮጀክቶችን ለማከናወንም ወደ 100 ቢሊየን ብር እንደሚጠይቅ አንስተዋል።

አሁን ላይ በኢኮኖሚ ሪፎርሙ ምክንያት በመንግስት ላይ የተፈጠረው የወጪ ጫና በታሪክ ትልቁ እንደሆነ አመላክተው÷ በ2018 በጀት ዓመት የገቢ ምንጩን የሚያሳድግበት ስራ ይሰራል ብለዋል።

የመንግስት የ2018 ረቂቅ በጀት 1 ነጥብ 93 ትሪሊየን ብር ሆኖ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቅረቡ ይታወሳል።

በታሪኩ ለገሰ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!