ቢዝነስ

በክልሉ ከ9 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

By Adimasu Aragawu

July 01, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ባለፉት 11 ወራት ከ9 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል።

የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ህይወት አሰግድ በበጀት ዓመቱ 10 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ በ11 ወራት ከ9 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ተናግረዋል።

በዚህም 57 በመቶ የክልሉን ወጪ በገቢ መሸፈን መቻሉን አንስተዋል።

በክልሉ መንግስት በተመደበ 20 ሚሊየን ብር 70 የታክስ ማዕከላትን የማደራጀት ስራ መሰራቱን ጠቁመዋል።

ግብር ከፋዩ ማሕበረሰብ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ከእንግልት በፀዳ መልኩ አገልግሎት እንዲያገኝ ለማስቻል 68 ማዕከላትን በቴክኖሎጂ እንዲተሳሰሩ ማድረግ ተችሏልም ነው ያሉት።

በኦዲት ግኝት ከ200 ሚሊየን ብር በላይ ለመንግስት ገቢ መደረጉን ገልጸው÷ የሥነ ምግባር ችግር የታየባቸው 132 ባለሙያዎች ላይ የዲስፕሊን፣ የፅሑፍ ማስጠንቀቂያ እንዲሁም ከሥራ የማሰናበት ርምጃ ከመውሰድ ባለፈ በወንጀል እንዲጠየቁ መደረጋቸውንም አብራርተዋል።

በተራመድ ጥላሁን

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!