ስፓርት

ሞናኮ አንሱ ፋቲን በውሰት አስፈረመ

By Adimasu Aragawu

July 01, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፈረንሳዩ ክለብ ሞናኮ ስፔናዊውን የፊት መስመር ተጫዋች አንሱ ፋቲን በውሰት ውል አስፈርሟል፡፡

ሞናኮ ስፔናዊውን የፊት መስመር ተጫዋች በ11 ሚሊየን ዩሮ የመግዛት አማራጭ ባካተተ የውሰት ውል ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል፡፡

በ2024/25 የውድድር ዓመት አንሱ ፋቲ ለባርሴሎና በሁሉም ውድድር 10 ጨዋታዎች ላይ ተሳትፏል፡፡

የ22 ዓመቱ ስፔናዊ የፊት መስመር ተጫዋች አንሱ ፋቲ በባርሴሎና ቤት እስከ 2028 የሚያቆይ ኮንትራት እንዳለው ይታወቃል፡፡

አንሱ ፋቲ በውሰት ውሉ መሰረት በሞናኮ እስከ ሰኔ 2026 ድረስ የሚቆይ ይሆናል፡፡

ከካታላኑ ክለብ ባርሴሎና በውሰት ውል ሞናኮን የተቀላቀለው አንሱ ፋቲ በሞናኮ ቤት 31 ቁጥር ማልያን እንደሚለብስም ተረጋግጧል፡፡

የፈረንሳዩ ክለብ ሞናኮ በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ፖል ፖግባ፣ ኤሪክ ዳየር እና አንሱ ፋቲን በማስፈረም ቡድኑን የማጠናከር ስራ አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!