የሀገር ውስጥ ዜና

የውጭ ሀገር ዜጎች የማይንቀሳቀስ የመኖሪያ ቤት ባለቤት የመሆን መብት አዋጅ ፀደቀ

By Adimasu Aragawu

July 01, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ሀገር ዜጎች የማይንቀሳቀስ የመኖሪያ ቤት ባለቤት የመሆን መብት አዋጅን አጸደቀ።

በምክር ቤቱ የከተማ፣ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በአዋጁ ዙሪያ ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡለት ጥያቄ ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥቷል።

መሬት የመንግስት እና የህዝብ እንደመሆኑ ለኢንቨስትመንት የሚመጡ ዜጎች መሬቱን የመሸጥ እና የመለወጥ መብት የላቸውም ብለዋል።

የኢትዮጵያዊያንን መብት በማይነካ መልኩ የውጭ ሀገር ዜጎች የመኖርያ ቤት ባለቤት በመሆን ኢንቨስትመንት ላይ እንዲሰማሩ ሥራዎች ይሰራሉ ነው ያለው ቋሚ ኮሚቴው።

የውጭ ሀገር ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ ገብተው በመኖሪያ ቤት ባለቤትነት ላይ ኢንቨስት እንዲያደርጉ የተቀመጠው የገንዘብ መጠን 150 ሺህ ዶላር ነው።

የቀረበው የገንዘብ መጠን አነስተኛ መሆኑ የተነሳ ሲሆን የተቀመጠው የገንዘብ መጠን አሁን በኢትዮጵያ ካለው የቤት ገበያ ጋር በማነፃፀር የወጣ ስለመሆኑም ተብራርቷል።

የተቀመጠው የገንዘብ መጠን 150 ሺህ ዶላር ሲሆን በጊዜ ሂደት ግን እየተሻሻለ እንደሚሄድም ተመላክቷል።

የውጭ ሀገር ዜጎች በመኖሪያ ቤት ባለቤትነት ላይ ኢንቨስት እንዲያደርጉ የቀረበው የገንዘብ መጠን ዝቅተኛ በመሆኑ ወደ ኢትዮጵያ በብዛት ሊገቡ ስለሚችሉ የሰው ቁጥሩ በሀገራችን እንዲጨምር ሊያደርግ ይችላል የሚል ጥያቄ ከአባላቱ ተነስቷል።

በዚህ ላይ ምላሽ የሰጡት የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ መሀመድ አብዶ (ፕ/ር)፥ በዚህ ኢንቨስትመንት ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ የውጭ ዜጎች ባል፣ ሚስት እና ልጆችን ብቻ ያካተተ አዋጅ በመሆኑ የህዝብ ቁጥሩ ሊበዛ አይችልም ብለዋል።

የሚመጡት ኢንቨስተሮች ከአዲስ አበባ ውጪ መስራት ቢፈልጉ በወጣው መመሪያ መሰረት ክልሎች ተፈፃሚ እንደሚያፈርጉም ተገልጿል።

በወንድማገኝ ጸጋዬ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook WMCC TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!