የሀገር ውስጥ ዜና

በፓሪስ ፎረም ላይ ኢትዮጵያ ምን አለች…

By Adimasu Aragawu

July 01, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከሰሞኑ ፈረንሳይ 12ኛውን የፓሪስ ፎረም አካሂዳለች።

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በፎረሙ የብድር ሂደት ማሳለጥን አንኳር አድርገዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው በፎረሙ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት÷ በሀገራት መካከል ያለው የብድር ሂደት ቀልጣፋ እንዲሆን መደበኛ የመግባቢያ ስምምነት (MoU) እንዲዘጋጅ ሐሳብ አቅርበዋል።

በዚሁም በቡድን 20 ሀገራት የጋራ ማዕቀፍ ስር የዕዳ አያያዝን በተመለከተ የኢትዮጵያን ልምድ አካፍለዋል።

በአበዳሪ ሀገራት የእዳ ማሻሻያ ድርድር ሂደት ገንቢ እና የትብብር አካሄድ መኖሩን በማንሳት የኢትዮጵያ አጋሮች ላደረጉት ድጋፍና ትብብርም ምስጋና አቅርበዋል።

በሂደቱ ውስጥ ያጋጠሙትን ተግዳሮቶች በመገንዘብ የወደፊት መፍትሔዎችን በተመለከተ ተግባራዊ ምክረ ሐሳቦች አቅርበው÷ ግልጽና ሊተነበይ የሚችል የጊዜ ሰሌዳ መኖሩ ለተበዳሪ ሀገራት የዕዳ እፎይታን እንዲያገኙ ያደርጋልም ነው ያሉት።

ሂደቱን የበለጠ ቀልጣፋ እንዲሆን ለማድረግና አላስፈላጊ መዘግየቶችን ለማስወገድ መደበኛ የመግባቢያ ስምምነት (MoU) እንዲዘጋጅም ነው ሐሳባቸውን ያቀረቡት።

በአበዳሪ እና በተበዳሪ ሀገራት መካከል ግልጽነት ሊኖር እንደሚገባ አንስተው÷ የተሳካ የእዳ አያያዝ በሁሉም አካላት የጋራ ቁርጠኝነት ላይ የተመሰረተና የጋራ የኃላፊነት ስሜት መፍጠር እንደሚያስፈልግ ማስረዳታቸውንም ኢዮብ (ዶ/ር) ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡

በቡድን 20 አባል ሀገራት የጋራ ማዕቀፍ የእዳ አያያዝ ተጠቃሚ የሆነችው ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ መጋቢት 2025 ከኦፊሴላዊው አበዳሪዎች ኮሚቴ ጋር በመርህ ደረጃ ስምምነት ላይ የደረሰች ሲሆን÷ የመግባቢያ ሰነድ ፊርማ በቅርቡ እንደሚከወን ይጠበቃል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!