የሀገር ውስጥ ዜና

ፌደራል ፖሊስ ከኢንተርፖል ጋር ያለውን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ቁርጠኛ ነው

By Adimasu Aragawu

July 03, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከኢንተርፖል ጋር ያለውን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ቁርጠኛ ነው አሉ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል።

ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረ ሚካኤል ከዓለም አቀፉ ፖሊስ ድርጅት (ኢንተርፖል) ፕሬዚዳንት ሜጀር ጀነራል አህመድ ናስር አልራይዚን ጋር ውይይት አድርገዋል።

ውይይታቸው ኢትዮጵያና ኢንተርፖል ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በመከላከል በኩል ትብብራቸውን ይበልጥ ማጠናከር ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።

ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ በዚሁ ወቅት÷ ኢትዮጵያ ከኢንተርፖል ጋር በመተባበር ያከናወነቻቸው ተግባራት ውጤታማ መሆናቸውን አንስተናል።

ድንበር ዘለል ወንጀሎችን በጋራ በመከላከል ረገድ የተገኙ ውጤቶችን ይበልጥ ማጠናከር የሚያስችሉ እና የአቅም ግንባታ ትብብርን ለማስፋት የጋራ መግባባት መፈጠሩንም ተናግረዋል።

የኢንተርፖል ፕሬዚዳንት ሜጀር ጀነራል አህመድ ናስር በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ ከኢንተርፖል ጋር ባላት ትብብር ውጤታማ እና ንቁ ተሳትፎ እያደረገች መሆኗን አንስተዋል።

ከውይይቱ በተጓዳኝ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በለውጡ ያከናወናቸውን ዘመናዊ አሰራሮችና ቴክኖሎጂዎችን መጎብኘታቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

ኢትዮጵያ እ.አ.አ ከ1958 ጀምሮ የኢንተርፖል አባል በመሆን በጋራ እየሰራች ነው።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!