አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2017 በጀት ዓመት 37 ቶን የወርቅ ምርት ለውጭ ገበያ ቀርቧል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመንግስትን የ2017 የዕቅድ አፈጻጸም አስመልክቶ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ነው፡፡
በማብራሪያቸውም ኢትዮጵያ ከፍተኛ የማዕድን አቅም ያላት ሀገር መሆኗን አውስተው÷ ይሁን እንጂ በቀደሙ መንግስታት ለዘርፉ ትኩረት ሳይሰጠው መቆየቱን ተናግረዋል፡፡
አሁን ላይ በዘርፉ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው÷ በ2017 በጀት ዓመት 37 ቶን የወርቅ ምርት ለውጭ ገበያ መቅረቡን አስረድተዋል፡፡
ባለፈው በጀት ዓመት አራት ቶን ወርቅ ብቻ ወደ ውጪ ተልኮ እንደነበር ጠቁመው÷ በዘንድሮው ዓመት በዘርፉ ከፍተኛ እመርታ መመዝገቡን አብራርተዋል፡፡
በዘርፉ ለውጭ ገበያ ከቀረበ ምርትም 3 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ገቢ ተገኝቷል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፡፡
በመላኩ ገድፍ