አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የምርምርና ልማት ስራን በተሟላ መልኩ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል የብሔራዊ ደህንነት ኮንፈረንና የምርምር አውደጥናት እየተካሄደ ነው።
አውደጥናት “በደህንነትና ስትራቴጂክ ጉዳዮች የሰለጠኑ ብቁ አመራሮችን በማፍራት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም እናስከብራለን” በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ የሚገኘው።
አውደጥናቱ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ምርምርና ልማት ሥራ ላይ ያሉ መልካም አጋጣሚዎችና ተግዳሮቶች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።
በመከላከያ ሠራዊት ወታደራዊ ምርምርና ልማት ዘርፍ ላይ ያለውን ገፅታ ለመቀየርና ፈጣን ለውጥ ለማምጣት የሚያስችሉ ስራዎች በዕቅድ መሰራት እንዳለባቸው ተጠቁሟል፡፡
የኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች በውይይቱ ወቅት እንደገለፁት፤ ተመራማሪዎች ምርምር ለማድረግ ብቃት እንዲኖራቸው የሚያስችሉ ሁኔታዎችን መፍጠር ያስፈልጋል።
የመከላከያ የምርምር ተቋማትን ትስስርና አደረጃጀት የሚያጠናክር ስርዓትም መፈጠር እንዳለበት ተነስቷል።
የብሔራዊ ደህንነት ኮንፈረንስ እና የምርምር አውደጥናቱን ያዘጋጀው የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ነው።
በየሻምበል ምህረት
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!