የሀገር ውስጥ ዜና

በምዕራብ አርሲ ዞን በ99 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባ ንፁህ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ለአገልግሎት ክፍት ሆነ

By Yonas Getnet

July 03, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን ነጌሌ አርሲ ወረዳ በ99 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባ ንፁህ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።

የክልሉ ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ኤባ ገርባ በዚሁ ወቅት÷ የሚመረቁ ፕሮጀክቶች የማህበረሰቡን ችግር ከመቅረፍ ባሻገር አብሮ የመኖር መስተጋብርን ያእንደሚያሳድጉ ጠቁመዋል።

የአካባቢው ነዋሪዎችም የውሃ ፕሮጀክትና የአካባቢያቸውን ሰላም እንዲጠብቁ አስገንዝበዋል።

የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ አህመድ ሀጂ በበኩላቸው÷ በዞኑ 681 ፕሮጀክቶች በ6 ቢሊየን ብር ተገንብተው እንደሚመረቁ ገልጸው፤ ተጠናቀው በአግባቡ ለማህበረሰቡ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

ፕሮጀክቱ ከ22 ሺህ 600 በላይ ማህበረሰብን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ የሚያደርግ እንደሆነ ተመላክቷል።

በወረዳ በማህበረሰቡ ተሳትፎ በሶላር የሚሰራ የውሃ መሳቢያ በ6 ሚሊየን 300 ሺህ ብር ወጪ ተገንብቶ ስራ ጀምሯል።

በዚህም ከ13 ሺህ በላይ የአካባቢው ሕብረተሰብ የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ እንደሚሆን ተጠቁሟል።

በጀማል ከዲሮ