የሀገር ውስጥ ዜና

5ኛው የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ነገ ቀጥሎ ይካሄዳል

By Melaku Gedif

July 04, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በየሳምንቱ ቅዳሜ ከአስገራሚ ተወዳዳሪዎች ብቃት ጋር የቀጠለው ደማቁ 5ኛው የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ የድምጻውያን ውድድር ነገም ቀጥሎ ይካሄዳል።

በውድድሩ የምድብ ሁለት ተወዳዳሪዎች እዮቤል ጸጋዬ፣ ካሳሁን ዘውዱ፣ ብሩክ ሰለሞን፣ ናሆም ነጋሽ፣ አብርሃም ማርልኝ ፣ ሱራፌል ደረጀ እና ናሆም ካሳዬ በቀጥታ ሥርጭት ይፎካከራሉ፡፡

በዕለት አቀራረብ መሰረት በሚያደርገው የፋና ላምሮት ውድድር ላይ በዳኞች እና በተመልካቾች ድምጽ በየሳምንቱ አንድ ተሰናባች ይኖራል።

በነገው 5ኛው የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር አንድ አንጋፋና ተወዳጅ ሙዚቀኛ በክብር እንግድነት ይታደማል።

ውድድሩን በፋና ቴሌቪዥን እና በሁሉም የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች በቀጥታ ሥርጭት መከታተል ይቻላል፡፡

በአጠቃላይ ለፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ከ3 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ሽልማት ተዘጋጅቷል፡፡

በ13ኛው ሳምንት አራት ምርጥ ተወዳዳሪዎችን ይዞ የፍጻሜ ውድድሩን የሚያካሂደው ፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር የዋንጫ እና የአዲስ ሙዚቃ ሽልማትንም ያበረክታል።

በለምለም ዮሐንስ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!